Latest News

ImageImageImageImage

በአርበኛ ሰለሞን ታከለ የተሰየመው አዳራሸ ዘመናዊ ወንበር የተገጠመለት መኾኑን የጃናሞራ ወረዳ ባሕል ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ

ደባርቅ:-ግንቦት 18/2017 ዓ.ም
(የሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን)

ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ በአርበኛ ሰሎሞን ታከለ / በቅጽል ስሙ አስጨናቂ/ ተሰይሞ የወረዳው ሕዝብና አስተዳደር ምክር ቤት ለሀገር የሚጠቅሙ ወሳኝ አጀንዳዎችን የመከረበት ታሪካዊ አዳራሽ ነው። ለበርካታ ዓመታት በመቀመጫነት ሲያገለግል የነበረው ደረቅ ወንበር ሲኾን በዚህ በጀት ዓመት ግን ከዩኤንዲፒ / UNDP/ ፕሮጀክት በተገኘ 4,241041 ብርና ከአስተዳደር ምክር ቤቱ 3,793,975 ብር በማስመደብ 243 ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ወንበሮች እንደተገጠሙለት የወረዳው ባሕል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ቄስ መሳፍንት አማረ አስታውቀዋል። የግድግዳ ቀለም፣ ኮርኒስ፣ መብራትና የመሳሰሉት በመጠገን አዳራሹን የማስዋብ ሥራዎች ማከናወናቸውን ገልጸዋል።

የቱሪዝም ኃላፊው እንደሚሉት የወንበሮቹ የአገልሎት ጊዜያቸው እንዲራዘም ፅዳተኛ በኩንትራ ተቀጥሮ በአግባቡ ቢጸዳ፣ የልብስ በጀት ተይዞ እንዳይቋሽሽ ቢሸፈን፣ የአዳራሹ ዙሪያ በቆርቆሮ ቢታጠር የሚል አስተያየትም አክለዋል። ለሥራው መሳካት ርብርብ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን የሥራና ሥልጠና ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ ደገፋው ታከለ ፣ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

2025-05-29 (504)